አዲስ ስደተኛ በኖርዌይ

የኖርዊጂያን ቋንቋ ትምህርት

Foto fra et norskkurs

የኖርዊጂያን ቋንቋ ትምህርት መብት እና ግዴታ

አንዳንድ ስደተኞች የኖርዊጂያን ቋንቋ ትምህርት እና የህብረተሰብ ትምህርት በነፃ የማግኘት መብት እና ግዴታ አላቸው። ይህም የሚመለከተው፣

 • ስደተኞችን
 • በሰብአዊ ምክንያት የመኖሪያ ፍቃድ ያገኙ ሰዎች
 • ጠቅላላ ጥገኝነት ላገኙ ሰዎች
 • ከላይ ከተጠቀሱት ጋር በቤተሰብነት የተቀላቀለ
 • ከኖርዊጂያን ወይም ከስኬንድናቪያን ሀገሮች ነዋሪዎች ጋር በቤተሰብነት የተቀላቀለ
 • ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ካለው ሰው ጋር አንድ ሰው ሲቀላቀል

ከ16-67 አመት ዕድሜ ያላቸው ሰዎች ብቻ በኖርዊጂያን የቋንቋ ትምህርት ላይ የመካፈል መብት እና ግዴታ አለባቸው። ይህም መብት እና ግዴታም በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ የ600 ሰዓት ትምህርትን መከታተልን ያካትታል። ከዚህም ሰዓት ውስጥ 50 ሰዓት ተማሪዎች በሚገባቸው ቋንቋ የህብረተሰብ እውቀት ትምህርትን ይማራሉ። ተጨማሪ ኖርዊጂያን የቋንቋ ትምህርት በነፃ የመማር እድልም አለ። እነዚህም ሰዓቶች እንዳስፈላጊነቱ የሚከፋፈሉ ሲሆን፣ በጠቅላላው ግን 3000 ሰ ዓት አይበልጡም።

የኖርዊጂያን የቋንቋ ትምህርት የመማር ግዴታ

የተወሰኑት የኖርዊጂያን የቋንቋ ትምህርት በነፃ የማግኘት መብት የላቸውም። ነገር ግን ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድን ለማግኘት የ300ሰዓት የኖርዊጂያን የቋንቋ እና የህብረተሰብ እውቀት ትምህርትን መከታተል ግዴታአለባቸው ።

 • አዉሮፓ ኢኮኖሚ ትብብርና ከአዉሮፓ ነጻ ንግድ ማህበር አገር ዉጪ የመጡ የስራ ፍለጋ ስደተኞች
 • ከነዚህ ጋር በቤተሰብነት ለመቀላቀል ወደ ሀገሪቱ የመጡ ሰዎች

ለኖርዊጂያን የቋንቋ ትምህርት መብትም ሆነ ግዴታ የሌላቸው።

የተወሰኑት የነፃ የኖርዊጂያን የቋንቋ ትምህርት መብትም ሆነ ግዴታ የላቸውም። ይህም የሚመለከታቸው፣

 • ተማሪዎች
 • ባህልን ለመማር የመጡ (አዉ ፔር)ና ሌሎች በጊዜያዊ ፍቃድ የሚቆዪ
 • የስካንዲኔቪያ ዜጎች
 • በአዉሮፓ ኢኮኖሚ ትብብርና በአዉሮፓ ነጻ ንግድ ማህበር ደንብን መሰረት በማድረግ መኖሪያ ፍቃድ ያላቸዉ።

መረጃ

የኖርዊጂያን ቋንቋ ኮርስ

በኖርዌይ የሚኖሩ ሁሉ ኖርዊጂያን ቋንቋ መናገርና መረዳት ይኖርበታል። የኖርዊጂያን ማህበረሰብ የሚጠብቀው ሁሉም ሰው በማህበረሰቡ ውስጥ መሳተፍንና በአብዛኛው ሰው ወደ ሥራ ተሰማርቶ ራስን መርዳት እንድችል ነው። በአብዛኛው ወረዳዎች የኖርዊጂያን ቋንቋ ትምህርት የሚሰጡ ሲሆን ሌሎችም ብዙ የግል የቋንቋ መማሪያዎች አሉ። አንዳንድ ስደተኞች ከወረዳው ነፃ የቋንቋ ትምህርት የምያገኙ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ከፍለው መማር አለባቸው። ይህም በመኖሪያ ፍቃድ ዓይነት ላይ የተመረኮዘ ነው።

መልመጃዎቹን ይስሩ