አዲስ ስደተኛ በኖርዌይ

የአገር ማላመጃ ፕሮግራም

    በኖርዌይ አገር ያላቸዉን ዕድል ለማሻሻል ወደ ኖርዌይ ከሚመጡት አዲስ ስደተኞች ዉስጥ ለተወሰኑት በአገር ማላመጃ ፕሮግራም ዉስጥ እንዲሳተፉ የኖርዌይ ፓርላማ አንድ ህግ አወጣ (የ አገር ማላመጃ ህግ)። የአገር ማላመጃ ፕሮግራም ወደ ኖርዌይ ማህበረሰብ መግቢያ ሲሆን ለፕሮግራሙ ሃላፊነት ያለዉ ወረዳ (ኮሙነ) ነዉ። የአገር ማላመጃ ፕሮግራሙ ስደተኞቹ በስራና በህብረተሰቡ ዉስጥ ያላቸዉን ተሳትፎ እንዲጨምሩ ይረዳል። ዓላማዉ የስደተኞችን በኢኮኖሚ ራስን መቻል ለማጠናከር ነዉ። አንዳንድ ስደተኞች በአገር ማላመጃ ፕሮግራም ዉስጥ የመሳተፍ መብትና ግዴታ አላቸዉ፤ ሁሉንም ግን አይመለከትም። እነዚህ ቡድኖች በአገር ማላመጃ ፕሮግራም የመሳተፍ መብት እና ግዴታም አላቸው።

    • ስደተኞች
    • በሰብአዊ ርህራሄ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች
    • ከላይ ከተጠቀሱት ሁለቱ ቡድኖች ጋር በቤተሰብነት የተቀላቀለ ሰው
    • በትዳር ዉስጥ በደል ደርሶባቸዉ ራሱን በቻለ ምክንያት የመኖሪያ ፍቃድ ያገኙ

ይህም መነሻዉ አንድ ሰዉ መሰረታዊ የሆነ ስለጠና ሲያስፈልገዉ ነዉ።

 

መረጃ

የማላመጃ ፕሮግራም የሚረዳው

 • ስደተኞች በሥራና በማህበራዊ ኑሮ እንዲሳተፉ እድል ይፈጥራል
 • የስደተኞችን በኢኮኖሚ ራስን መቻልን ያጠናክራል
 • በኖርዊጂያን ቋንቋ መሰረታዊ እውቀት እንዲያገኙ ይረዳል
 • ስለ ኖርዊጂያን ማህበረሰብ መሰረት ይሰጣል

መልመጃዎቹን ይስሩ