ትምህርትና የሙያ ማረጋገጫ

ከፍተኛ ትምህርት

ተማሪዎች በክፍል ትምህርት ውስጥ
ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በሗላ ተማሪዎች ለከፍተኛ ትምህርት በዩኒቨርሲቲ ወይም በኮሌጅ ደረጃ መቀጠል ይችላሉ።
ብዙዎቹ ዩኒቨርሲቲ ወይም በኮሌጅ የመንግስት ሲሆኑ ትምህረቱም ለተማሪዎች በነፃ ነው። ወጪውን የሚሸፍነው መንግስት ነው። ተማሪዎች ግን ትንሽ የሴሚስተር ክፍያ ወይንም የመመዝገቢያ መክፈል የተለመደ ነው። የግል ኮሌጆችም አሉ። እዚህ ተማሪዎች የተጠቃሚ ክፍያ ለትምህርታቸው ይከፍላሉ።
የመንግስት ትምህርት ቤቶችንና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ወጪ መንግስት ሲከፍል ትምህርቱም ለህዝቡ ነፃ ነው። ነገር ግን በመንግስትም ሆነ በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ተማሪዎች እራሳቸው ለትምህርታቸው የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውንም የትምህርት እቃዎች እራሳቸው ሟሟላት አለባቸው። ይህም ሲባለ እራሳቸው የመማሪያ መፅሃፍትና የመገለገያ እቃዎችን እራሳቸው መግዛት አለባቸው ማለት ነው።
ምንም እንኳን ዩነቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ነፃ ቢሆኑም ለአንዳንድ ወጪዎች መሸፈኛ የሚሆን ገንዘብ ያስፈለጋል። ስለዚህም ገንዘብ ከመንግስት የተማሪዎች መማሪያ ከዝና በመበደር የቤት ኪራይን፣ ምግብና አንዳንድ አስፈላጊ ነገሮችን ትምህርት ላይ ባሉበት ወቅት መክፈል የተለመደ ነው። በዚህም መልኩ ከቤተሰብ እርዳታ ውጪ ሁሉም ይህን የሚፈልግ ሰው የከፈተኛ ትምህርቱን መማር ይችላል። በተጨማሪም ብዙ ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ስራ በመስርት በቂ ገንዘብ በማግኘት ኑሮአቸውን ይመራሉ።

እኩል ደረጃ ያላቸው የትምህርት እድል አንድ ዘመናዊ ማህበረሰብ በሰራተኞች፣

እኩል ደረጃ ያላቸው የትምህርት እድል
አንድ ዘመናዊ ማህበረሰብ በሰራተኞች፣ በቴክኖሎጂ፣ በምርትና በአዲስ ፈጠራ ላይ የተመሰረት ነው። ስለዚሀ ኖርዌይም ከፍተኛ ትምህርት የተማሩ ማህበረሰብ ትፈልጋለች። ይህንንም መንግስት እኩል ደረጃ ያላቸው የትምህርት እድል ለሁሉም በማቅረብ አስተዋፆ ያደርጋል።

በኖርዌይ በዛሬው ጊዜ 27 በመቶ የሚሆኑ አዋቂዎቸ የከፍተኛ ትምህርት አላቸው። ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ወጣቶቸ የከፍተኛ ትምህርት የሚማሩ ሲሆንና በኖርዌይ የትምህርት ደረጃም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በዛሬው ጊዜ 60 በመቶ የሚሆኑት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ሴቶች ሲሆኑና ከወንዶችም ሴቶች ትንሽ በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ይበልጧቸዋል።
ሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ማረጋገጫ ያላቸው በሙሉ በኮሌጅ ወይም በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ቦታ እንዲያገኙ ማመልከት ይችላሉ።
የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ቦታዎችን የሚያድለው የምደባ ቢሮ (ሳሞርድና ኦፕታክ) የሚባል ድርጅት ነው። Samordna opptak

መረጃ

የመንግስት የትምህርት ብድር

የትምህርት ብድር ድርጅት በኖርዌይ ለሚማሩት ለተማሪዎች በዉጪ ለሚማሩት የኖርዊጂያን ተማሪዎች ድጋፍና ብድር ይሰጣል።

የትምህርት ብድር ድርጅት ለሚከተሉት ለዉጥ ይረዳል።

  • ይህም ሁሉም ሰው በአከባቢ፣ በእድሜ፣ በጾታና በኢኮኖሚ ሳይለይ በእኩልነት ትምህርት እንድያገኙ ይረዳል።
  • የትምህርት ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ትምህርቱ በአጥጋቢ የሥራ ሁኔታ መካሄድ አለበት።
  • ማህበረሰቡ የተማረ የሥራ ኃይል እንዲያገኝ ዋስትና መስጠት።

ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርት አዋቂዎችም ከትምህርት ብድር ድርጅት ብድርና ድጋፍ ማግኘት ይችላል።

መልመጃዎቹን ይስሩ